=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
የሰው ልጅ ከተፈጠረበት ጀምሮ ማለትም አደም አለይሂ ሰላም ወደዚች አለም ሲመጣ ከአሏህ ዘንድ የነገራቶችን ስሞችና እውቀትን አሏህ ችሮት ነው። ከዚህም አልፎ ለነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የመጨረሻው ወህይ (ቁርአን) ሲገለፅላቸው የመጀመሪያው ቃል «ኢቅራ» አንብብ የሚል ነበር። ይህም ምን ያህል እውቀት በኢስላም ያለውን ቦታ የሚያመላክት ነው....Read more
በሽምግልና እድሜ የሚገኝ እውቀት ልክ በውሃ ላይ እንደሚፅፍ ሰው ሲሆን በወጣትነት ጊዜ የሚገኝ እውቀት ደግሞ ልክ በድንጋይ ላይ እንዳለ ማህተም ነው።
በወጣትነት እድሜ እውቀትን መሻት አስፈላጊ የሚያደርገው ነገር የጊዜ ጉዳይ ነው። እውቀትን መሻት አትኩሮት ፣ ድግግሞሽ የሚፈልግ ሲሆን ለዚህ ደግሞ ምቹ ጊዜ የወጣትነት እድሜ ነው....Read more
ንባብ በሂወታችን ውስጥ ትልቅ ቦታ ሊኖረው የሚገባ መሠረታዊ ክህሎት ነው። በተሰማራንበት ነገር ሁሉ ስኬታማ ለመሆን ፣ በእምነታችን ጠንካራ ለመሆን ፣ እምነታችነን ሙሉ ለማድረግ እንዲሁም ደስተኛና የተረጋጋ ሂወት ለመምራት እራሳችነን በእውቀትና በጥበብ ልንክን ይገባል።
ይህን ለማድረግ ደግሞ የንባብ ክህሎታችን መግራት ይጠበቅብናል። ወጣቶች አብዛሃኛውን ጊዜ የምናሳልፈው በትምህርት በመሆኑ በትምህርታችን ጐበዝ ለመሆንና በቂና ተፈላጊውን እውቀት ይዘን ለመውጣት የንባብ ክህሎታችንን ከወዲሁ ልናነሻሽል....Read more
ሁሉም ሰው በሂወት ዘመኑ መለወጥና የለውጡን ነፀብራቅ ማየት ይሻል። ይህም ማለት በፊት ከነበረበት ሁኔታ በእውቀቱ ፣ በጤናው ፣ በኢማኑ ፣ በትዳሩ ፣ በማህበራዊ ኑሮው ፣ በስብዕናውና በስራ ልምዱ ለውጥን ማየት ይሻል። ይህን የምንሻው ለውጥ ግን ዝም ብለን እየተነፈስንና ያገኘነውን እየተመገብን በመኖር ብቻ የሚገኝ አይደለም። ይህን ለውጥ ለማግኘት መንቀሳቀስ መጀመርና ስራዎቻችነን በትጋት እንዲሁም በእቅድ መስራት ይኖርብናል።
ለውጥን ያለ ስራ ማሰብ ቂልነት ነው። ለውጥን ለማምጣትና ፍሬዋንም ለመቅመስ ግቦችን ቀርፀን ስራዎቻችነን በታታሪነት መስራት....Read more
ውድ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ እንደሚታወቀው የዚች አለም ኑሮ ጊዜያዊና ጠፊ ነው። ታዲያ እኛ ደግሞ ዝምብለን አልተፈጠርንም። ማለቴ አሏህ በቁርአኑ እንደገለፀው እኛ የተፈጠርንበት አላማ አሏህን በብቸኝነት ልንገዛ ነው።
ይህ በዚህ እንዳለ አሏህን በብቸኝነት ለመገዛት ፣ እምነታችነን ሙሉ ለማድረግ እውቀት የመልካም ስራዎቻችን የጀርባ አጥንት በመሆኑ ዛሬ ላይ የእውቀት የመሠረት ዲንጋይ ልንጥል ግድ ነው። ይህን ለማድረግ አላማችነን መንደፍና ጊዜያችነን....Read more
ንባብ በህይወታችን ልናዳብረው እና ልናሳድገው የሚገባ እጅግ ጠቃሚ ክህሎት ሲሆን ጠቀሜታውም በትምህርታችን ወይም በተሰማራንበት የስራ ዘርፍ ስኬታማ ለመሆን ብቻ ሳይሆን በዕለት ተዕለት ኑሯችን ስኬታማ ለመሆን ወሳኝ ክህሎት ነው።
የሚከተሉት ጠቇሚ ነጥቦች የንባብ ጊዜያችነን እና የንባብ ክህሎታችነን ለማሳደግ የሚረዱን....Read more
በአእምሯችን የሚንሸራሸሩ ሃሳቦች በሂወታችን ለሚከሰቱ ነገሮች ሁሉ ምክኒያት ናቸው። ሃሳባችን በባህሪያችን እና በዝንባሌያችን ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥር ሲሆን ተግባራችነን ይቆጣጠራል። ስለምናስበው ነገር....Read more
መምህርት: ናማሙሽ እስቲ በካርታው ላይ አሜሪካን አሳየኝ?
ማሙሽ: ይህችት ቲቸር
መምህርት: ጎበዝ ልጆች! አሜሪካን ማን እንዳገኛት ታውቃላችሁ?
ልጆች: ማሙሽ ነው ያገኛት ቲቸር
መምህርት: 'ሀ'ን እያሳየች ይህች ምንድ ናት ልጆች?....Read more
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|